ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከቦትስዋና ፕሬዚዳንት ዱማ ቦኮን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቦትስዋና ፕሬዚዳንት ዱማ ቦኮን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከፕሬዚዳንቱ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል ብለዋል፡፡
ወይይቱ በቀጣናዊ ጉዳዮች ለተሻለ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ያሉ እድሎች እና አፍሪካን ቀጣይ የሚመራ ትውልድን ማብቃት ላይ በምንሰራበት ጉዳይ ዙሪያ ተወያይተናል ነው ያሉት፡፡