ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለደንበኞቹ የ57 ሚሊየን ብር ሽልማት አዘጋጀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ‘በሽ’ የተሰኘ የሽልማት መርሐ ግብርን በዛሬው እለት በይፋ አስጀምሯል።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አንዷለም አድማሴ (ዶ/ር) በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ እንዳሉት፥ ኩባንያው ለደንበኞቹ የ57 ሚሊየን ብር ሽልማት አዘጋጅቷል፡፡
መርሐ ግብሩ ለሶስት ወራት የሚዘልቅ ሲሆን፥ ሽልማቶቹ ከእያንዳንዱ ደንበኛ የአጠቃቀም ልምድ ጋር የተሰናሰሉ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
በሽልማት መርሐ ግብሩ የማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ላይ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት የ1 ሚሊየን ብር አሸናፊዎች ሽልማታቸውን ተቀብለዋል፡፡
ኩባንያው የደንበኞችን ግላዊ የአጠቃቀም ፍላጎት በመረዳት ለእያንዳንዱ የደንበኞች የአጠቃቀም ልምድ የሚመቹ የግል ጥቅሎችን እንደሚያቀርብም ተናግረዋል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለደንበኞቹ በሚስማማ መንገድ አዳዲስ አገልግሎቶችን ይዞ ቀርቧልም ነው ያሉት።
በየሻምበል ምህረት