Fana: At a Speed of Life!

ጅቦችን የሚያናግረው ኢትዮጵያዊ…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ22 ሚሊየን በላይ ተከታይ ያለው ናስ ዴይሊ የተሰኘ የፌስቡክ ማሕበራዊ ትስስር ገጽ ኢትዮጵያዊውን የጅቦች መጋቢ አባስን ተዋወቁት ሲል ጽፏል፡፡
አባስን የሐረር ከተማ ነዋሪ እንደሆነ የሚገልጸው ናስ ዴይሊ÷ በአንድ ወቅት ጅቦች ለአካባቢው ስጋት እንደነበሩ ያትታል፡፡
ከዓመታት በፊት የአካባቢው ነዋሪዎች ራሳቸውንና እንስሶቻቸውን ለመከላከል ከጅቦች ጋር ይፋለሙ እንደነበር በማስታወስ የአባስ ወላጅ አባት ጅቦቹን ከመፋለም ይልቅ አንድ ለየት ያለ ነገር እንደሞከሩ ይጠቅሳል፡፡
ይህም ጅቦቹን በየምሽቱ መመገብ መሆኑንና በሂደትም የጅቦቹን እምነት ማግኘት መቻላቸውን አንስቷል፡፡
በዚህም ጅቦቹ የአካባቢው ስጋት መሆናቸው ቀርቶ አሁን ላይ ከአካባቢው ሰዎች ጋር ተስማምተው በሰላም እንደሚኖሩ የናስ ዴይሊ መረጃ ያመላክታል፡፡
አባስ ጅቦችን መመገብ ከወላጅ አባቱ በመውረስ ማታ ማታ ጅቦችን በመመገብ ከጎብኚዎች ገንዘብ የማግኘት ስራውን ተያይዞታል ሲል አመልክቷል።
ይህን ያልተለመደ የሰዎች እና የጅቦችን ሰላማዊ ግንኙነት ለመጎብኘት ከመላው ዓለም በርካታ ቱሪስቶች አካባቢውን እንሚጎበኙም ናስ ዴይሊ ጠቁሟል፡፡
አንዳንዴ መከባበር በሰዎች እና አራዊት መካከል ያለውን ግንኙነት በዚህ መልኩ ሲቀይር ይስተዋላል ሲልም አስገንዝቧል፡፡
በአቤል ነዋይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.