ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብን መረቁ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2017 (ኤፍ ኤ ምሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያውያን ሕብረ ብሔራዊነት መገለጫ የሆነውን ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ በዛሬው ዕለት መረቁ፡፡
የኢትዮጵያውያን የዘመናት ቁጭት የነበረው ታላቁ ኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ የምረቃ ሥነ ሥርዓት በጉባ እየተካሄደ ነው፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተገኝተዋል፡፡
በተጨማሪም በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ የቀድሞ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮች ታድመዋል፡፡