የአማራ ክልል ሕዝብ ቃሉም ተግባሩም ለልማት የወገነ መሆኑን አሳይቷል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ሕዝብ ቃሉም ተግባሩም ለልማት የወገነ መሆኑን አሳይቷል አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ ሕዳሴ ከሁሉም ማዕዘናት ወደ አንድ ሀገራዊ የልማት ዕሳቤ እየተደመሩ ኃያል የመሆን እና የመተባበር ህያው ምልክት ነው ብለዋል።
ዛሬ በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች ሕዝቡ ያሳየው ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ ገጸ ብዙ ትርጉም ያለው ሰልፍ መሆኑን አንስተው÷ በዚህም የክልሉ ሕዝብ ቃሉም ተግባሩም ለልማት የወገነ መሆኑን አሳይቷል ነው ያሉት፡፡
በአማራ ክልል የተስተዋለው የዛሬው ሰልፍ እንደዓባይ ለታላቅ ግብ የመደመር፣ ፈተናዎችን እያሸነፉ መሻገር፣ ለልማት የተከፈለን መስዋዕትነት የማክበር የከበረ የሕዝብ ድምጽ መሆኑን አመልክተዋል።
እንደዚህ ያሉ የሕዝብ ታላላቅ ሰልፎች ለቀጣይ የኢትዮጵያ ግዙፍ ልማቶች የሚያተጋን የብርታት ደወል ነው ሲሊም ገልጸዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!