Fana: At a Speed of Life!

የጤና መድህን አገልግሎት በፍትሃዊነት ለማድረስ በትኩረት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ የጤና መድህን አገልግሎትን በፍትሃዊነት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት፡፡
አገልግሎቱ ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ እና ከአምርፍ ጤና አፍሪካ ጋር በመተባበር በ2018 የእቅድ አተገባበር ላይ ያተኮረ መድረክ በሀዋሳ ከተማ አካሂዷል።
የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ላምሮት አንዱአለም በመድረኩ ላይ እንዳሉት፥ በሀገር ደረጃ 63 ሚሊየን ዜጎች የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን በፍትሃዊነት ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፥ በቀጣይ የተጠቃሚዎችን ቁጥር ለማሳደግ ክልሎች በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
ባለፈው ዓመት አገልግሎቱን ለማቅረብ ከተገልጋዮች ከተሰበሰበው 19 ቢሊየን ብር በተጨማሪ 7 ቢሊዮን ብር በመንግስት መሸፈን ተችሏል ነው ያሉት።
በተያዘው ዓመት በጤና መድህን አገልግሎት ላይ ጥራት ለመጨመር እንደሚሰራ ገልጸው፥ ህብረተሰቡ በቅድሚያ ክፍያ መፈጸም እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በበኩላቸው፥ በክልሉ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት አሰጣጥ እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት 72 በመቶ ያህሉ የክልሉ ነዋሪዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ነው ኃላፊዋ የገለጹት፡፡
በደብሪቱ በዛብህ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.