Fana: At a Speed of Life!

የመስቀል ደመራ በዓል የሚከበርበትን ስፍራ የማጽዳት መርሐ ግብር ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስቀል ደመራ በዓል የሚከበርበት የመስቀል አደባባይ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ዛሬ ጠዋት የማጽዳት መርሐ ግብር ተከናውኗል።
በመርሐ ግብሩ በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ወንድሙ ሴታን (ኢ/ር) ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የተለያዩ እምነት ተከታይ ወጣቶችና የጽዳት ሠራተኞች ተሳትፈዋል።
ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የመስቀል ደመራ በዓል ከኢትዮጵያ አልፎ የዓለም ቅርስ የሆነና የአብሮነት በዓል ነው።
በመሆኑም ሃብትነቱ ከእምነቱ ተከታዮች ባሻገር የመላው ኢትዮጵያውያን መሆኑን ነው የገለጹት።
በዚህም ከተማ አስተዳደሩ የመስቀል ደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር የተለያዩ ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል።
የዛሬው የጽዳት መርሐ ግብርም የዚሁ አካል መሆኑን ጠቁመው ÷ አሁን ላይ በዓሉ በድምቀት እንዲከበር የዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቃቸውን አመልክተዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.