Fana: At a Speed of Life!

ለኪነ ጥበብ ፈጠራ ምቹ ማዕከላትን እየገነባን ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለኪነ ጥበብ ፈጠራ ምቹ ማዕከላትን እየገነባን ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአዲስ አበባ ሕጻናት እና ወጣቶች ቴአትር እና ሲኒማ ኮምፕሌክስን መርቀው ከፍተዋል።

በዚህ ወቅትም ዘመኑን ዋጅቶ የተገነባው ማዕከሉ መንግስት  ለኪነ ጥበብ ዘርፍ  የሰጠውን ትኩረት ያመላክታል  ብለዋል።

ማዕከሉ  የአዳጊዎች ሕልም የሚጎለብትበት፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች በቴአትርና በሲኒማ ጎልተው የሚወጡበት የልህቀት ሥፍራ እንደሚሆን አመልክተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን  ከያንያን ማእከሉን የአዲስ አበባን እና የኢትዮጵያን ገጽታ እንዲያስተዋውቁበት አደራ ሰጥተዋል።

መንግስት በባህል፣ በፈጠራ እና በብሔራዊ ኩራትና ትርክት ግንባታ ላይ የጀመርነውን ሥራ አጠናክሮ  እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.