ኢሬቻ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ እንዲከበር መገናኛ ብዙኃን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮ ኢሬቻ በዓል ሀገራዊ አንድነትን በሚያጸና እና በሚያጠናክር መልኩ እንዲከበር መገናኛ ብዙኃን የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
የኢሬቻ በዓል አከባበርን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች በተሰጠው ገለጻ ላይ የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሀይሉ አዱኛ እንዳሉት፥ የኦሮሞ ህዝብ ባህል እና እሴት ምንጭ ለዘመናት ሲተዳደርበት የቆየው የገዳ ስርዓት ነው።
ከእነዚህ ባህል እና እሴቶች መካከል አንዱ የሆነው የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ህዝብ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት መሆኑን ገልጸው፤ ዘንድሮ ‘ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት’ በሚል መሪ ቃል ይከበራል ብለዋል።
የምስጋና እና የእርቅ በዓል የሆነውን ኢሬቻ ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ እንዲከበር የመገናኛ ብዙኃን ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የበዓሉን ምንነት፣ እሴቶች እና የአከባበር ሁኔታውን በተመለከተ ግንዛቤ መፍጠር እንዳለባቸው አመልክተዋል።
ኢሬቻ የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያዊያን በዓል ነው ያሉት ኃላፊው፤ መገናኛ ብዙኃን በዓሉን ወንድማማችነትን በሚያሳይ መልኩ ሊዘግቡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም ኢሬቻ በቱሪዝም ዘርፍ ለሀገር የሚያበረክተውን ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦ እና ለሀገር ገፅታ የሚኖረውን ጥቅም የሚያጎላ ሽፋን መስጠት አለባቸው ብለዋል።
ኢሬቻ የምስጋናና የእርቅ በዓል እንጂ የፖለቲካ ማራመጃ መድረክ እንዳልሆነም ተናግረዋል።
የኢሬቻ በዓል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት እንዲመዘገብ የጋራ ጥረት ያስፈልጋል ብለዋል።
በዓሉ በድምቀት እንዲከበር ከኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት እና ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት መደረጉን ተናግረዋል።
በሚኪያስ አየለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!