የኢንቨስትመንት ፍቃድ የወሰዱ አልሚዎች የስራ እንቅስቃሴን በጥብቅ ዲሲፕሊን መምራት ይገባል – አቶ ኦርዲን በድሪ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢንቨስትመንት ፍቃድ የወሰዱ አልሚዎች የስራ እንቅስቃሴን በጥብቅ ዲሲፕሊን መምራት ይገባል አሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ።
የክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ የኢንቨስትመንት ማዕድንና ኢነርጂ ፅ/ቤት አንደኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል።
ፅ/ቤቱ ባቀረበው ሪፖርት በክልሉ በኢንቨስትመንት ፍቃድ መሬት ወስደው ወደ ስራ ባልገቡ አልሚዎች ላይ ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ እስከ ኢንቨስትመንት ፍቃድ ስረዛ ርምጃ መወሰዱን አመላክቷል።
በመድረኩ አቶ ኦርዲን በድሪ እንዳሉት፤ የኢንቨስትመንት ፍቃድ የወሰዱ አልሚዎች የስራ እንቅስቃሴን ልዩ ትኩረት በመስጠት በጥብቅ ዲሲፕሊን መምራት ይገባል።
በክልሉ በኢንቨስትመንት ለተሰማሩ አልሚዎች ድጋፍ ለማድረግ መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸው፤ አልሚዎች ላይ ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ለይቶ ለመፍታት ይሰራል ብለዋል።
ለኢንቨስትመንት መሬት ወስደው ወደ ስራ ያልገቡ አልሚዎች ላይ ክትትል በማድረግ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ርዕሰ መስተዳድሩ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ሃላፊ ሔኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!