Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን እድገት ለማረጋገጥ ለግብርና ትምህርት ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል – አረጋ ይርዳው (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን እድገት ለማረጋገጥ ለግብርና ትምህርት ትኩረት መስጠት ይገባል አሉ የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር)፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ ኢትዮጵያ በርካታ የተፈጥሮ ሃብቶች፣ አምራች ዜጋ እና የቆየ ስራ ባህል እንዳላት አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብቷ ለግብርና ስራ ምቹ መሆኑን ጠቅሰው÷ ለአውሮፓ እና ለእስያ አህጉር የሚቀርብ የመሬት አቀማመጧ ለወጪ ንግድ ምቹ ሁኔታ መሆኑንም አብራርተዋል።

የሕዝብ ብዛት ተጨማሪ አቅም እና ሃብት በመሆኑ አምራች ኃይሉ አዳዲስ ዕውቀት እንዲቀስም በማድረግ ወደ ስራ ማስገባት ይቻላል ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ ግብርናን ጨምሮ በዘመናት ሂደት ያዳበረቻቸው ክህሎቶች አላት ያሉት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር)፤ ከራሷ አልፋ ሌሎችን እንድትረዳ የግብርና ትምህርት ላይ ትኩረት በማድረግ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የአርሶ አደሩ ልጅ ከቤተሰቡ የግብርና እውቀት እንደሚያገኝ ጠቅሰው፤ ይህንን እውቀት በማዘመን የግብርና ምርታማነትን ማሳደግ ይቻላል ብለዋል፡፡

በብርሃኑ አበራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.