ከፌደራል የጸጥታ ኃይል ጋር በሚናበብ መልኩ የፖሊስ ተቋም ሪፎርም እየተሰራ ነው – አቶ አረጋ ከበደ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በክልሉ የሚሰጡ ተልዕኮዎችን ለመወጣት እና ከፌደራል የጸጥታ ኃይል ጋር በሚናበብ መልኩ የፖሊስ ተቋም ሪፎርም እየተሰራ ነው አሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ።
አቶ አረጋ ከበደ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ሪፎርም አካል የሆነ የዘመናዊ ህንጻ ምርቃት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ በክልሉ ያለው የጸጥታ አካላት ሪፎርም የሀገር አቀፉ ሪፎርም አካል እንደሆነና የአደረጃጀትና አሰራር ለውጥ ማምጣትን ያካተተ መሆኑን ተናግረዋል።
የአማራ ከልል ፖሊስ ለክልሉ ሰላም እና አንድነት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከተ መሆኑን አንስተው÷ በዚህም ተልዕኮን መሰረት ባደረገ መልኩ አሰራሩን በመገምገም መሰራቱን ጠቁመዋል።
የክልሉን ፖሊስ አደረጃጀት በማስተካከል ብቁ እና ተልዕኮ ፈጻሚ እንዲሆን በአማራ ክልል ምክር ቤት ቀርቦ የፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ ጸድቆ እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።
የክልሉ የሚሊሻ ኃይልም የሪፎርም ተግባር አካል ሆኖ እየተተገበረ መሆኑን ገልጸው÷ የጸጥታ ኃይሉ አቅም ሕዝብ በመሆኑ ሕዝባዊ መሰረት እንዲኖረው ለማድረግ ትኩረት ተሰጥተው እየተሰራ እንደሚገኝም አመላክተዋል።
በለይኩን ዓለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!