Fana: At a Speed of Life!

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ያስገነባው የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አቀፍ ሬዲዮ ጣቢያ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ያስገነባው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አቀፍ ሬድዮ ጣቢያ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
‎
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ደገላ ኤርጌኖ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ‎ሬዲዮ ጣቢያው ዩኒቨርሲቲው የሚሰራቸውን ሥራዎች እንዲሁም የአካባቢውን ማህበረሰብ ባህልና እሴት ለሌሎች ለማስተዋወቅ ፋይዳ አለው።
‎
‎ዩኒቨርሲቲው በምርምር እና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እንዲሁም በመማር ማስተማር ዘርፉ እያከናወነ ያለውን ተግባር ጨምሮ አካባቢያዊና ዓለም አቀፍ መረጃዎችን ተደራሽ ያደርጋልም ነው ያሉት።
‎
‎የሬዲዮ ጣቢያ ስቱዲዮ ዘመኑን የሚመጥን የሚዲያ ቴክኖሎጂን ያሟላ መሆኑ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሀገሪቱ በሚዲያው እንዱስትሪ ያካበተውን አቅም የሚያሳይ እንደሆነና ተቋሙ በዘርፉ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቀጣይነት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ጠቁመዋል።
‎
‎የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዶኒያስ ወ/ዓረጋይ በበኩላቸው÷ የሬዲዮ ጣቢያው ፋና በሚዲያ እንዱስትሪ ያካበተውን ልምድ ወደ ማህበረሰብ የማውረድ ሥራን እየሰራ ለመሆኑ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።
‎
ኮርፖሬሽኑ በሚዲያ ቴክኖሎጂ ዘርፍ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት በመላ ሀገሪቱ ሰፊ ስራን እያከናወነ እንደሚገኝና በቀጣይም በሌሎች አካባቢዎች መሰል የማስፋፋት ስራዎችን እንደሚሰራ አመላክተዋል።
‎
‎ከዩኒቨርሲቲው ጋር ያለው የአብሮነት ስራ እንደሚቀጥል እና የባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበት የሚረዱ ሥልጠናዎችም እንደሚሰጡ አቶ አዶኒያስ ተናግረዋል።
‎
በ‎ፍሬው አለማየሁ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.