በጎንደር ከተማ ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን ለማስተካከል ዲጂታል አሰራሮች ተግባራዊ እየተደረጉ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጎንደር ከተማ ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን ለማስተካከል ዲጂታል አሰራሮች ተግባራዊ እየተደረጉ ነው አሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኛው።
አቶ ቻላቸው የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት እያካሄደ ባለው መደበኛ ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት ነው ይህንን ያሉት።
በከተማው መደበኛ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን አንስተው÷ ከመሬት ጋር በተያያዘ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን ለማስተካከል ዲጂታል አሰራሮች ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሆነና ከ1 ሚሊየን በላይ ፋይሎች በዚሁ ሥርዓት መካተታቸውን ተናግረዋል።
በተለያዩ ምክንያቶች የዘገዩ ፕሮጀክቶች መንግሥት በሰጠው ትኩረት ጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሆኑ በማንሳት የአዘዞ ጎንደር የአስፓልት መንገድ ስራ እና የመገጭ ግድብ ፕሮጀክት ስራ በዚህ ዓመት እንዲጠናቀቁ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
እንዲሁም የከተማውን ገቢ ለማሳደግ በተደረገው ጥረት ባለፈው ዓመት ከሁለት ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰበሰቡን ገልጸው÷ በዚህ ዓመት 5 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን አመላክተዋል።
ከፀጥታ ስራ ጋር በተገናኘ በከተማው በቀደመው ጊዜ የነበረው የእገታና ሌሎች የወንጀል ድርጊቶች አሁን ላይ መሻሻል ማሳየቱን እና በዚህ ተግባር የተሳተፉ 52 የፀጥታና የፖለቲካ አመራሮች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጋቸውን ነው ያብራሩት።
በከተማዋ የሚገኙ ቅርሶችን የመጠገን ስራው በጥሩ መንገድ መከናወኑን ገልጸው÷ ከ85 ሺህ በላይ ጎብኚዎች የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን እንደጎበኙ ጠቅሰዋል።
በከተማዋ የኮሪደር ልማት ስራውም ውጤታማ ሁኖ እየተመራ መሆኑን አንስተዋል።
በምናለ አየነው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!