Fana: At a Speed of Life!

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት የክብር ዶ/ር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል፡፡

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.