የኑሮ ውድነትን የማረጋጋትና ከተረጂነት የመላቀቅ ግቦችን ለማሳካት …
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኑሮ ውድነትን የማረጋጋትና ከተረጂነት የመላቀቅ ግቦችን ለማሳካት የባለድርሻ ተቋማት ቅንጅት ሊጠናከር ይገባል አሉ የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ።
የብልጽግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ በመንግሥት ሥራዎች አፈጻጸም ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን÷ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የተከናወኑ ሥራዎችና የተገኙ ውጤቶች እንዲሁም ከተረጂነት የመላቀቅ ግቦች በአጀንዳነት ቀርበዋል፡፡
አቶ አደም ፋራህ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የኑሮ ውድነትን ማረጋጋትና ሥራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት የሚሹ አንገብጋቢ አጀንዳዎች ናቸው፡፡
ከተረጂነት መላቀቅ የተሟላ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መንገድ መሆኑን ገልጸው÷ በዚህ ላይ በተቀናጀ አግባብ መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ሦስቱንም ሀገራዊ ግቦች በተሟላ መልኩ ለማሳካት የባለድርሻ ተቋማት ቅንጅት ሊጠናከር እንደሚገባ ነው የገለጹት፡፡
በአፈጻጸም ደረጃ እንደ ሀገር ውጤቶች መገኘታቸውን ጠቁመው÷ያለውን የአፈጻጸም ልዩነት ለማጥበብ መስራት እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል፡፡
በዘርፉ ውጤታማነትን ለማሳደግ በጋራ ማቀድ እና አፈጻጸሞችን በጋራ በጥልቀት መገምገም ይገባል ማለታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!