Fana: At a Speed of Life!

ቱሪዝም ሚኒስቴር “ጉዞ ወደ ሀገር ቤት” የተሰኘ መርሐ ግብር ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቱሪዝም ሚኒስቴር በጉዲፈቻ ተወስደው በውጭ ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን “ጉዞ ወደ ሀገር ቤት” የተሰኘ መርሐ ግብር ይፋ አድርጓል።

መርሐ ግብሩ በጉዲፈቻ ተወስደው በባህር ማዶ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውንና ቅርሶችን እንዲጎበኙ እንዲሁም በልዩ ልዩ ባህላዊ ክንዋኔዎች በመሳተፍ የሀገራቸውን ብዝሃባህል እንዲያውቁ  ለማስቻል ያለመ ነው።

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ መርሐ ግብሩ በጨቅላ እድሜያቸው ማንነታቸውንና መነሻቸውን ሳያውቁ በጉዲፈቻ ወደተለያዩ ሀገራት የተወሰዱ ኢትዮጵያውያን ወደ እናት ሀገራቸው እንዲመለሱ እድል ለመስጠት የተዘጋጀ ነው።

ባህላቸውን፣ ማንነታቸውንና ታሪካቸውን እንዲያውቁ ከማድረግ ባሻገር ወላጆቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ማግኘት እንዲችሉና ያላቸውን እውቀት እንዲያካፍሉ መርሐ ግብሩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

መርሐ ግብሩን ቱሪዝም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ቱሪዝም ኮሚሽን፣ ከየሃረግ ኦዲዮ ቪዲዮ ፕሮዳክሽን እና በስዊድን ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በትብብር  እንዳዘጋጀው ተገልጿል፡፡

በየሻምበል ምህረት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.