የመገጭ ግድብ የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመገጭ መስኖ ልማት ፕሮጀክት የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ በጎንደር በነበረን ጉብኝት የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የሥራ ሁኔታ ገምግመናል ብለዋል።
ፕሮጀክቱ 870 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ÷ ሥራው ሲጠናቀቅ 17 ሺህ ሔክታር በመስኖ አቅርቦት ይሸፍናል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስረድተዋል፡፡
የፕሮጀክቱ ቁልፍ የሆነው የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ ቀሪ ሥራዎችም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ እየተካሄዱ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።
የመገጭ መስኖ ልማት ፕሮጀክት በሚጠናቀቅበት ወቅት የአካባቢውን የግብርና ምርታማነት የሚያሳድግ ይሆናል ሲሉም አመልክተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!