አየር መንገዱን የሚመጥን የአቪዬሽን ደኅንነት አገልግሎት ሰጪ ተቋም እየተገነባ ነው – አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድን የሚመጥን የአቪዬሽን ደኅንነት አገልግሎት ሰጪ ተቋም እየተገነባ ነው አሉ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ አዲስ ያስገነባውን ባለ አምስት ወለል የቢሮ ህንጻ ዛሬ አስመርቋል።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በአቪዬሽን ደኅንነት ዘርፍ በተከታታይ ዓመታት በተከናወኑት የሪፎርም ተግባራት በቴክኖሎጂ፣ መሠረተ ልማት፣ ሰው ኃይል፣ የአሠራር ሥርዓቶችን በማሻሻል እና በማዘመን በአፍሪካ ምርጥ የአቪዬሽን ደኅንነት አገልግሎት ሰጪ ተቋም እየተገነባ ይገኛል፡፡
የአየር መንገዱ አገልግሎት እየሰፋ ከመሄዱ አንጸር ይህንኑ የሚመጥን ዝግጁነት መኖሩን በመግለጽ÷ የሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ የሪፎርም ሥራዎች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል ለአቪዬሽን ዘርፉ አገልግሎት ምቹ የሆነ ሁለገብ ህንጻ ተገንብቷል ብለዋል።
የአገልግሎቱ ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ሲሳይ ቶላ በበኩላቸው÷ በሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ዘርፍ የተከናወነው ሪፎርም ኢትዮጵያን እንደ ታላቅነቷ የሚመጥን የአቪዬሽን ደኅንነት አገልግሎት ሰጪ ተቋም እንዲገነባ መሰረት የጣለ መሆኑን ተናግረዋል።
የአቪዬሽን ደኅንነት ስምሪት ከዘመኑ ጋር ፈጥኖ መገኘትን እንደሚያስፈልግ በመግለጽ÷ የተመረቀው ሕንጻ ዘመኑ የሚጠይቀው ቴክኖሎጂ የተሟሉለትና ለወደፊቱም ተለዋዋጭ የቴክኖሎጂ ሁኔታዎችን ታሳቢ በማድረግ የተገነባ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሕንጻው ከአፍሪካ ምርጥ የአቪዬሽን ደኅንነት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል አንዱ ለመሆን የተያዘውን ስትራቴጂክ ግብ እውን ለማድረግ የሚያግዝ ነው ያሉት ደግሞ የሲቪል አቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ አስራት ቀጀላ ናቸው።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዓለም አቀፍ መስፈርትን መሰረት ያደረገ የደኅንነት አገልግሎት በመስጠት አየር መንገዱ የአፍሪካ ኩራት ሆኖ የመሪነት ደረጃውን እንዲይዝ የጀርባ አጥንት ሆኖ የበኩሉን ተቋማዊ ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ማታቸውን አገልግሎቱ ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ አመላክቷል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!