Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል የቱሪዝም አቅም ይበልጥ ለማጎልበት የሚረዱ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል የቱሪዝም አቅም ይበልጥ ለማጎልበት የሚረዱ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው አሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፡፡

አቶ አደም ፋራህ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በነበራቸው ቆይታ በርካታ የክልሉን የቱሪዝም አቅም ይበልጥ ለማጎልበት የሚረዱ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን አይቻለሁ ብለዋል።

ለአብነትም የአፋርን ማንነት፣ ባህል፣ ጀግንነትና ጽናት ከዘመናዊ ሥነ ሕንፃ ጋር አዋህደው የያዙ በርካታ ሆቴሎችና አዳራሾች ተገንብተዋል፣ እየተገነቡም ይገኛሉ ነው ያሉት።

እነዚህ ለክልሉ የቱሪዝም ኮንፈረንስ መስክ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍቱ አስቻይ አቅሞች የብልጽግና ራዕይ የሚሰነቅባቸውና የአፋር ክልል የወደፊት ታሪክ የሚፃፍባቸው ከመሆን አልፈው አፋርን ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች የሚካሄዱበት ማዕከል ለማድረግ የሚያግዙ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች የተገኙ የልማት ውጤቶችን ማስመዝገብ እና ያየናቸውን የቱሪስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት መገንባት የሚችለው አንድነት፣ ሰላምና ትጋት ያለው ሕዝብና አመራር ብቻ ነው ሲሉም አመላክተዋል።

ስለሆነም የእስካሁኑን ውጤቶች ለማስቀጠልና ለማስፋት ለወደፊቱም ለሀገራችን በሚበጀው ሰላም፣ ልማት፣ መልካም አስተዳደርና ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ማጠናከር ላይ ይበልጥ መተባበርና በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በተለይ አመራሩ እንደ ብልጽግና ፓርቲ ከአፋር ሕዝብ የተሰጠንን እድልና የተጣለብንን አደራ በቅንነት፣ በታማኝነትና በላቀ ቁርጠኝነት ለመወጣት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንድቀጥል አደራ ማለት እፈልጋለሁ ሲሉም በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

በዚሁም ሰመራ ከተማ ከገባንበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ በላቀ የኢትዮጵያዊነት ስሜት፣ ጽናትና ጠንካራ ባህላዊ ስርዓት ከሚታወቀው ከተከበረው የአፋር ሕዝብና ከወንድሞቼና እህቶቼ የክልሉ አመራሮች ለተደረገልን ሞቅ ያለ አቀባበልና መስተንግዶ ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.