Fana: At a Speed of Life!

ሀገራቸውን ያገለገሉ ባለውለታዎች …

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራቸውን በሁለንተናዊ ዘርፍ በጀግንነት ያገለገሉ የሀገር ባለውለታዎችን ትውልድ ሊዘክራቸው ይገባል አሉ የቀድሞ ወታደር ደራራ ባይሣ፡፡

“ውትድርና የገራው ሕይወት” የተሰኘ የግል የሕይወት ታሪካቸው ላይ የተመሰረተ መጽሐፍ የጻፉት ደራራ ባይሣ በ1960 ዓ.ም አየር ወለድን በመቀላቀል በውትድርና ከዚያም በሌሎች ዘርፎች ሀገራቸውን አገልግለዋል፡፡

የቀድሞ ወታደር ከፋና ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የኢትዮጵያን ዕድገት እንደማይፈልጉ ትውልድ ጠንቅቆ ማወቅ አለበት ብለዋል።

በኢትዮጵያ ጀግኖች ልጆች ትግል ይህ የጠላት ሃሳብ እስካሁን እንዳልተሳካ አስረድተዋል፡፡

ዛሬ ለእነዚህ ሃይሎች ተላላኪ መሆን ነገ የታሪክ ጠባሳ ስለሚሆን ውስጣዊ አንድነት ላይ ትኩረት ማድረግ አለብን ነው ያሉት።

በጦር ሜዳ የተሰለፈ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የሙያ መስክ ጀግኖች የሀገር ባለውለታዎች እንዳሉ አንስተው፤ ይህም በትውልድ ግንባታ ውስጥ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ሀገር በትውልድ ቅብብሎሽ እንደምትገነባ ገልጸው፤ የትናንት ከሌለ የዛሬ ስለማይኖር ጀግኖችን መዘከር እና ሥራቸውን ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በብርሃኑ አበራ

የቀድሞ ወታደር ደራራ ባይሣ ከፋና ፖድካስት ጋር የነበራቸውን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡- https://www.youtube.com/watch?v=1n1m46A08KE

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.