ኢትዮጵያና አዘርባጃን ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ይሰራሉ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያና አዘርባጃን የፓርላማ፣ የህዝብ ለህዝብና የኢንቨስትመንት ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ይሰራሉ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ኤልቺን አሚርባዮቭን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይታቸውም÷ የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ህዝብ ለህዝብ ትስስር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
የሁለቱ ሀገራት ፓርላማዎች ትስስር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማጠናከር አጋዥ መሆኑ ተገልጿል።
አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ለረጅም ዓመታት የዘለቀና እየተጠናከረ የመጣ ነው።
ሁለቱ ሀገራት ሲቪል ሰርቪሱን ለማጠናከር እንዲሁም በትምህርት ዘርፍ በትብብር ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰው÷ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የሚያደርጓትን ተግባራት እያከናወነች እንደምትገኝ ጠቅሰዋል።
የአዘርባጃን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሰማሩ በጋራ እንሰራለንም ነው ያሉት።
አፈ ጉባዔው አዘርባጃን ኮፕ 29ን ማስተናገዷን አንስተው÷ ኢትዮጵያ የኮፕ 32ን በውጤታማነት እንድታስተናግድ አዘርባጃን ያላትን ልምድና ተሞክሮ እንድታጋራ ጠይቀዋል።
አምባሳደር ኤልቺን አሚርባዮቭ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያና አዘርባጃን ያላቸውን ትስስር የበለጠ ለማጠናከር እንሰራለን ብለዋል።
አዘርባጃን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ለዓመታት የዘለቀ ግንኙነት፣ የህዝብ ለህዝብ፣ የባህልና የንግድ ትስስር ለማጠናከር እንደምትሰራ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ለማስተናገድ በመመረጧ እንኳን ደስ ያላችሁ ያሉት አምባሳደር ኤልቺን÷ አዘርባጃን ኮፕ 32 በስኬት እንዲጠናቀቅ ሀገራቸው ያላትን ልምድና ተሞክሮ ለማጋራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!