10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሕዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሰመራ ሎጊያ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል፡፡
በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ጫልቱ ሳኒ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ ፎረሙ ከተሞች በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በመዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥ፣ በኮሪደር ልማት አተገባበር እና በሌሎች ዘርፎች ላይ ተሞክሮ የተለዋወጡበት ነበር፡፡
በከተማ የመሬት አጠቃቀም እና የቤት ልማት አያያዝን ለመቅረፍ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመው ÷ የከተሞች የልምድ ልውውጥን በማጠናከር ወደ ተሻለ ብልጽግና መሻገር ይገባል ብለዋል።
በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚነሳውን ቅሬታ መፍታት እንደሚገባ የተናገሩት ሚኒስተሯ÷ በሰመራ ሎጊያ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 10ኛው የከተሞች ፎረም ስኬታማ እንደነበር አመልክተዋል፡፡
ከ140 በላይ ከተሞች በተሳተፉበት ፎረሙ ከተሞች በ5 ምድቦች ተከፍለው ለየምድቡ በቀረቡ የመወዳደሪያ መስፈርቶች ተመዝነዋል።
በዚህም ከምድብ አንድ 1ኛ አዳማ ፣2ኛ ቢሾፍቱ ፣ 3ኛ ሀዋሳ በመሆን ሲያሸንፉ ÷ በምድብ ሁለት ደግሞ ጅማ ፣ ሆሳዕና እና ዲላ በቅደም ተከተል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡
የሸገር ከተማ በ10ኛው የከተሞች ፎረም ልዩ ተሸላሚ ሲሆን ÷ አዘጋጇ ከተማ ሠመራ ሎጊያም ሽልማት ተበርክቶላታል።
11ኛውን የከሞች ፎረም የአሶሳ ከተማ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡
በቤዛዊት ከበደ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!