የኢትዮጵያና ፈረንሳይ ግንኙነት ተጠናክሮ ቀጥሏል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ግንኙነት እየተከናወኑ ባሉ ትብብሮች ተጠናክሮ ቀጥሏል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተወይይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ ግንኙነት እየተከናወኑ ባሉ ትብብሮች መጠናከሩን ቀጥሏል ብለዋል፡፡
በዚህ ረገድ ከፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ትብብሮች ስላሉበት ደረጃ በትኩረት መምከራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡