የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለውጥ ማሳያዎች …
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ገ/መስቀል ጫላ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለውጥ ማምጣቱን የሚያሳዩ በርካታ ውጤታማ ስራዎች በየአካባቢው ተከናውነዋል አሉ።
በክልሉ ባለፉት ቀናት “በመደመር መንግሥት እይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሃሳብ በ2ኛ ዙር የተሰጠውን ሥልጠና ሲከታተሉ የቆዩ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የልማት ስራዎችን ተመልክተዋል፡፡
ጉብኝቱ አመራሮቹ በስልጠናው በንድፈ ሀሳብ ያገኙትን እውቀት በመስክ ምልከታ በተግባር ለማዳበር ያለመ ነው።
አቶ ገብረመስቀል ጫላ በወቅቱ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የሚጨበጥ ተስፋ ያላት ሀገር መሆኗን በመገንዘብ በሁሉም መስክ በትጋት መስራት ይገባል።
ያለውን ጸጋ በአግባቡ በመለየት በተደረገ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለውጥ እያመጣ መሆኑን የሚያሳዩ ውጤታማ ስራዎች አሉ ብለዋል።
አመራሮቹ የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብርን ጨምሮ በተለያዩ የልማት ኢኒሼቲቮች የተሰሩ ስራዎችን በወላይታ ሶዶ ከተማ የተመለከቱ ሲሆን፤ በከተማዋ 120 የወተት፣ 106 የዶሮ፣ 29 የስጋ እንዲሁም 5 የዓሣ መንደሮች ተመስርተው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረጉ እንደሆነ ተመላክቷል።
በከተማው ከሌማት ትሩፋት በተጨማሪ ሌሎች የልማት ስራዎችም ተስፋ ሰጪ እንደሆኑ ተገልጿል።
በመለሰ ታደለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!