በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢ የሕዝቦችን የልማት ተጠቃሚነት ለማጠናከር…
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር አካባቢ የሕዝቦችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማጠናከር በትብብር መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢ የሕዝቦችን የልማት፣ ሰላም እና መልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሲከናወን የቆየው ፕሮጀክት ማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡
በመርሐ ግብሩ የግብርና እና የሰላም ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን አመራሮች፣ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶችና የኬንያ መንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የሰላም ሚኒስትር አማካሪ አምባሳደር እሸቱ ደሴ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢ የሚኖሩ ሕዝቦች ተመሳሳይ ባህል፣ ቋንቋና የሕይወት መስተጋብር አላቸው፡፡
የሕዝቦችን ዘላቂ ሰላም ለማስጠበቅና ትስስራቸውን ይበልጥ ለማሳደግ ሁለቱ ሀገራት በትብብርና በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በአካባቢው የልማት፣ ሰላምና የመልካም አስተዳደር ሁኔታን ከማጠናከር ባለፈ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን ይበልጥ ለማሳደግም በትኩረት መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አበራ ዴሬሳ በበኩላቸው÷ በአካባቢው ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት በሚገባ ተጠቅሞ ለማልማት በትብብር እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በዚህ ረገድ ባለፉት ዓመታት ‘ቮለንተሪ ሰርቪስ ኦቨርሲስ (ቪኤስኦ) እና ሌሎች ሲቪል ማህበራት ከመንግስት ጋር በመቀናጀት ሲከናወን የቆየው ፕሮጀክት ውጤታማ እንደነበር ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡
በፕሮጀክቱ በአካባቢው የሚገኙ የሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች የንግድ ልውውጥ፣ የውሃና የግጦሽ መሬት አጠቃቀም፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመቆጣጠርና ሌሎች መስተጋብሮች እንዲሳለጡ አስችሏል ነው ያሉት፡፡
በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢ በቦረና፣ ማርሳቤትና ሌሎች አካባቢዎች ነዋሪዎች ሁለንተናዊ መስተጋብር እንዲጠናከር መስራት ይገባል ያሉት ደግሞ የቪኤስኦ ፕሮግራሞች ኃላፊ አዚኬል አስኪሱ ናቸው፡፡
ተቋማቸው የሁለቱን ሕዝቦች ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማጠናከርና የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከሀገራቱ መንግሥታት ጋር በቁርጠኝነት ያከናወነው ፕሮጀክት አመርቂ ውጤት ማምጣቱን አስረድተዋል፡፡
የፕሮጀክቱ ትግበራ የሀገራቱን መንግሥታት ፖሊሲ መሰረት አድርጎ መተግበሩን ጠቁመው÷ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች መጋራታቸውን አመልክተዋል፡፡
የቪኤስኦ ኢትዮጵያ ተወካይ ተመስገን አለሙ (ዶ/ር)÷ በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አካባቢ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ድርቅ፣ ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ጾታዊ ጥቃትና ሌሎች ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የባለድርሻዎች ትብብር አስፈላጊ ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!