ኢትዮጵያ ኮፕ32ን እንድታዘጋጅ መመረጧ የዲፕሎማሲ ውጤት ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባዔን (ኮፕ32) እንድታዘጋጅ መመረጧ የስኬታማ ዲፕሎማሲ ውጤት ነው አለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክቶ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ÷ ያለፉት ሳምንታት ስኬታማ ተግባራት የተከወኑበት ስለመሆኑ አንስተዋል።
በኮፕ30 እና የቡድን 20 አባል ሀገራት ጉባኤ ላይ ኢትዮዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን ያስጠበቀ ተሳትፎ ማድረጓን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ኮፕ32ን እንድታዘጋጅ መመረጧ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ለወሰደቻቸው ርምጃዎች እውቅና የሰጠ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲያቸውን በኢትዮጵያ እየከፈቱ ነው ያሉት አምባሳደር ነብያት÷ በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን የመመለሱ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አመላክተዋል።
በአሸናፊ ሽብሩ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!