Fana: At a Speed of Life!

43 ዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ጉባዔዎችን ያስተናገደው አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል…

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እስካሁን 43 ዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍና ሀገር አቀፍ ጉባዔዎችን በስኬት አስተናግዷል፡፡

የማዕከሉ የገበያና ጥናት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ቴዎድሮስ ገበያው ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ÷ ማዕከሉ አዲስ አበባን የኮንፈረንስ ቱሪዝም መዳረሻ ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፡፡

ትላልቅ ጉባዔዎችንና ሌሎች ሁነቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ ማስተናገድ የሚያስችል ሁለንተናዊ አቅም ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡

የጉባዔ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያን እንግዳ ተቀባይነት ባህል ባንጸባረቀ መልኩ ቀልጣፋና ዘመኑን የዋጀ ሁሉን አቀፍ አገልግሎት እንዲያገኙ በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

እስካሁን ድረስም 43 ዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍና ሀገር አቀፍ ጉባዔዎችን በስኬት ማስተናገድ መቻሉን ነው የገለጹት፡፡

ማዕከሉ ትላልቅ ጉባዔዎችን፣ ኤግዚቢሽኖችን፣ የንግድ ውይይቶችን፣ ባህላዊ ክዋኔዎችንና ሌሎች ሁነቶችን ዓለም አቀፍ ደረጃን በጠበቀ መልኩ ለማስተናገድ ሁሌም ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡

በፈረንጆቹ 2028 ድረስ የተለያዩ ሁነቶችን የሚያዘጋጁ አካላት ለማዕከሉ ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑንም አቶ ቴዎድሮስ ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም ጉባዔዎችንና ሌሎች መድረኮችን የሚያዘጋጁ አካላት ቦታ ለማስያዝ ቅድሚያ መመዝገብ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.