ስምረት ፓርቲ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለመወዳደር ዝግጅት እያደረገ ነው
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለመወዳደር ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅና ያገኘው ፓርቲ የምክር ቤቱን የመጀመሪያ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩም ፓርቲው ያለፉትን ስድስት ወራት ያከናወናቸውን የስራ አፈጻጸም መገምገምን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባልና የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኃላፊው አቶ ብርሃነ ገ/የሱስ ተናግረዋል።
የ7ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት ከአጀንዳዎች መካከል እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
በዚህም ለምርጫው የሚወዳደሩ ዕጩዎችን ለመምረጥ እና ቅስቀሳ ለማድረግ መዘጋጀቱን አንስተዋል።
ምንም እንኳን በትግራይ ክልል የደኅንነት ችግር ቢኖርም ሕዝቡ ይመራኛል የሚለውን አካል በሰላማዊ መንገድ እንዲመርጥ ፓርቲው የበኩሉን ይወጣል ብለዋል።
በነፃነት ፀጋይ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!