Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በመስቀል አደባባይ መልሶ ግንባታ ስራ ላይ እየተሳተፉ ላሉ አካላት ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመስቀል አደባባይ መልሶ ግንባታ ስራ ላይ እየተሳተፉ ላሉ አካላት ምስጋና አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ በመስቀል አደባባይ የሚካሄደውን ሥራ በወቅቱ ለማጠናቀቅ ሌት እና ቀን ለሚሠሩ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረስ ብለዋል።

ጠንክሮ መሥራት እና በትጋት ላይ የተመሠረተ ጠንካራ የሥራ ሥነ ምግባር የስኬት ምሦሶ ነው ሲሉም አንስተዋል።

ፋውንቴንና የተለያዩ መዝናኛዎችን ባካተተ መልኩ እየተገነባ ያለው የመስቀል አደባባይ መልሶ ግንባታ በለገሀር ቸርችል አደባባይ እስከ ፒያሳ ድረስ በሚሰራው አረንጓዴ ስፍራ ፕሮጀክት ጋር የተያያዘ ነው።

ግንባታው ለህዝባዊ አደባባይነት በሚመጥን መልኩ በዘመናዊ መልኩ እየተገነባ ሲሆን ቦታው ላይ ከመሬት በታች እስከ 1 ሺህ 400 ተሽከርካሪ ለማቆም የሚያስችል የመኪና ማቆሚያ ይገነባል ተበሏል።

ከመስቀል አደባባይ እስከ ፒያሳ ድረስ ያለው መንገድ ትይዩ በሆነ መልኩ የሚገነባ ሲሆን በመንገዶቹ ጠርዝ ያለው የእግረኞች መሄጃ ሰፋ ባለ መልኩ የሚገነባ መሆኑም ታውቋል።

የመንገዶቹ ጠርዝ ለአካል ጉዳተኞች እንዲመች ተደርጎ እንዲሁም የብስክሌት መጓጓዣን ባካተተ መልኩ እየተገነበ ነው የሚገኘው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.