Fana: At a Speed of Life!

ሜሲ የዓለም ዋንጫ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብረ ወሰንን ሰበረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእግር ኳስ ጥበበኛው ሊዮኔል ሜሲ በዓለም ዋንጫ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ አዲስ ታሪክ በመጻፍ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብረ ወሰንን መስበር ችሏል፡፡

ምሽት 2 ሰዓት ላይ መካሄድ በጀመረው እጅግ አስደናቂ ጨዋታ ላይ ሜሲ ክብረ ወሰን መስበር ያስቻለችውን ታሪካዊ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በዓለም ዋንጫ መድረክ ያስቆጠራት 17ኛዋ ግብ በጀርመናዊው ኮከብ ሚሮስላቭ ክሎዝ በ16 ግቦች ተይዞ የነበረውን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ታሪካዊ ክብረ ወሰን በይፋ የግሉ እንዲያደርግ አስችላዋለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.