Fana: At a Speed of Life!

ኢንስቲትዩቱ የኦሮሚያ ክልልን የስፓሻል መረጃ ትንተና ለመስራት ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ከኦሮሚያ ክልል ፕላንና ልማት ኮሚሸን ጋር የስፓሻል መረጃ ትንተና ለመስራት ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱ በክልሉ የጤና፣ የትምህርት፣ የቱሪዝም፣ የማዕድን፣ የመንገድ፣ የግብርና፣ የመስኖ፣ የውሃ እና የአይሲቲ ስፓሻል መረጃ ትንተና ለመስራት የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ስምምነቱን የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፖሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ በላቸው ፀሐይ እና የኦሮሚያ ክልል ፕላንና ልማት ምክትል ኮሚሽነር ሞገስ ቱፉ (ዶ/ር) በጋራ  ፈርመውታል፡፡

አቶ በላቸው ፀሐይ በዚህ ወቅት÷ አክለውም ከዚህ በፊት ኢንስቲትዩቱ ከተለያዩ የክልሉ ተቋማት ጋር በትብብር በርካታ ውጤታማ ስራዎችን መስራቱን ተናግረዋል፡፡

ስምምነቱ የስፓሻል መረጃን ማልማትና ለባለሞያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት፣ የክልሉን ኘሮጀክቶች በመተንተን እና ተደራሽነታቸውን በመለየት ለውሳኔ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

ሞገስ ቱፉ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ስምምነቱ የጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ የስፓሻል መረጃ አሰባሰብ እና ትንተና ዙሪያ የሚታዩ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚስችል ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ስምምነቱ እያደገ የመጣውን አዳዲስ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የክልሉ ሀብት በእቅድ እና በስርዓት እንዲመራ ብሎም ተደራሽነቱን ለመገምገምና ውሳኔ ለመስጠት የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.