Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሴቶች የፋይዳ መታወቂያ እንዲይዙ ለማስቻል …

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በተያዘው በጀት ዓመት በክልሉ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን የሚሆኑ ሴቶች የፋይዳ መታወቂያ እንዲይዙ ለማስቻል እየተሰራ ነው አለ።

‘የዲጂታል ፋይዳ መታወቂያ ለሁሉም ሴቶች እና ህፃናት’ በሚል መሪ ሀሳብ ቢሮው ያዘጋጀው የሩጫ ውድድር በሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል።

የቢሮው ኃላፊ እመቤት ኢሳያስ እንዳሉት፤ የክልሉ ነዋሪዎች የፋይዳ መታወቂያ እንዲይዙ በትኩረት እየተሰራ ነው።

ፋይዳ መታወቂያ ወሳኝ በመሆኑ በማህበረሰቡ ውስጥ ትልቅ ሚና ያላቸው ሴቶች የፋይዳ መታወቂያ ባለቤት እንዲሆኑ ለማስቻል በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

በዚህም በበጀት ዓመቱ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሴቶች የፋይዳ መታወቂያ እንዲይዙ የሚያስችል እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አሸናፊ ኤሊያስ በበኩላቸው፤ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት እየሰራን ባለንበት ወቅት ፋይዳ መታወቂያ ትክክለኛ መረጃ ለመያዝ ጠቃሚ ነው ብለዋል።

በክልሉ ዘንድሮ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች ፋይዳ መታወቂያ እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑን አንስተው፤ እስካሁን ከ1 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎች የፋይዳ መታወቂያ ባለቤት ሆነዋል ነው ያሉት።

በደብሪቱ በዛብህ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.