Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባን የኢንቨስትመንትና የንግድ ማዕከል በማድረግ ተወዳዳሪ የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባን የኢንቨስትመንትና የንግድ ማዕከል በማድረግ ተወዳዳሪ የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከንቲባዋ ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስመጥር ከሆነው ኬርፎር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፓትሪክ ላስፋርገስ እና የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ ጋር በከተማዋ ስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

በውይይታቸውም ኬርፎር ከሜድሮክ ኢንቨስመንት ግሩፕ ጋር በፈረመው ስምምነት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ የሚገባበትን ምቹ ሁኔታን በመጠቀም፣ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የንግድ ትስስሮችን ለማጠናከርና ሌሎችም ታዋቂ ዓለም አቀፍ ብራንዶችን ወደ ከተማዋ ለማምጣት በጋራ ለመሥራት መግባባታቸውን አመላክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.