Fana: At a Speed of Life!

22 ሚሊየን ሄክታር መሬት በተቀናጀ ተፋሰስ ማልማት…

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዘንድሮ ዓመት 22 ሚሊየን ሄክታር መሬት በተቀናጀ ተፋሰስ ይለማል አሉ የግብርና ሚኒስትር ዴዔታ ኢያሱ ኤሊያስ (ፕ/ር)።

ሚኒስትር ዴኤታው ከፋና ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት÷ ባለፉት አስርት ዓመታት በአፈር እና ውሃ ጥበቃ ሥራ ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል።

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የአፈር መሸርሸር ያለበት መልክዓ ምድር እንደሚገኝ ገልጸው÷ በዚህም ምክንያት በጎርፍ የሚሄደው አፈር የኃይል ማመንጫ ግድቦችን በደለል እንደሚሞላ ተናግረዋል።

ይህም ምርትና ምርታማነት፣ የኃይል ማመንጨት እና ሌሎች ሥራዎች ላይ ከፍተኛ ችግር እንደሚፈጥር በማንስት÷ በተሰራው የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ሥራ የአፈር መሸርሸር አደጋን መቀነስ እንደተቻለ አመላክተዋል።

በተሰራው ሥራም የአፈር መሸርሸር ምጣኔን ከ130 ቶን በሄክታር ወደ 54 ቶን መቀነሱን ገልጸው÷ በተፋሰስ ልማት፣ በአረንጓዴ ዐሻራና በመስኖ ሥራ በፍራፍሬ እና በአትክልት ምርት ከፍተኛ ውጤት እንደተገኘ ጠቁመዋል።

ባለፉት አመታት የተሰሩ 500 ሺህ ሄክታር ተፋሰሶችን ለመጠገን መታቀዱንም ገልጸዋል።

በብርሃኑ አበራ

ሚኒስትር ዴዔታው ከፋና ፖድካስት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ👇

https://www.youtube.com/watch?v=9m9zPchLmSw

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.