Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን በመሠረተ ልማት የማስተሳሰር ተልዕኮ ተጠናክሮ ይቀጥላል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያን በመሠረተ ልማት ማስተሳሰርና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን የመገንባት ተልዕኮውን አጠናክሮ ይቀጥላል አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡

የደብረ ማርቆስ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት፥ የአውሮፕላን ትራንስፖርት አገልግሎቱ መጀመር የአካባቢውን ቱሪዝምና ንግድ የበለጠ እንደሚያሳልጥ ይጠበቃል፡፡

ደብረ ማርቆስ ከ60 ዓመታት በፊት አውሮፕላን ማረፊያ እንደነበራት አስታውሰው፥ ለዘመናት ካገለገለ በኋላ እንዲቋረጥ በመደረጉ ሕዝቡም በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ቆይቷል ነው ያሉት፡፡

የለውጡ መንግሥት ይህ የሕዝብ ጥያቄ ትክክለኛ መሆኑን በመገንዘብ ምላሽ መስጠቱን ገልጸዋል፡፡

የመደመር መንግሥት ተልዕኮ ኢትዮጵያን በመሠረተ ልማት ማስተሳሰርና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን መገንባት መሆኑን ገልጸው፥ ይህን ተልዕኮውን በሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.