የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 118 ተማሪዎች አስመረቀ
አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 118 ተማሪዎች አስመረቀ።
ዩኒቨርሲቲው በድህረ ምረቃና በቅድመ መደበኛ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቀው።
ከተመራቂዎች መካከል 56ቱ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ሲሆኑ 23 ተማሪዎች ደግሞ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሰለጠኑ የህክምና ዶክተሮች እንዲሁም በቴክኖሎጂ ኢኒስቲቲዩት 39 ተማሪዎች በኪነ ህንፃ በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸው ናቸው፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተመራቂዎች ሃገራችን በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ውስጥ ሆና የተመረቁ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ በተለይም የህክምና ተመራቂዎች የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በተጀመረው ጥረት ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
ሎችም በተመረቁበት ሙያ የሃገሪቱን ብልፅግና በማረጋገጥ ረገድ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር ኡባህ አደም በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት በመሰማራት በ2012 በጀት ዓመት 38 የምርምር ስራዎች ፀድቀው ወደ ስራ መግባታቸውንና ሃያ ሰባቱ መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል።
በተሾመ ሃይሉ