Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባን የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል ለማድረግ የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት እንዲሁም የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል ለማድረግ የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

ከንቲባዋ በአዘርባጃን ባኩ ከተማ በሚካሄደው የዓለም ከተሞች ፎረም ላይ አዲስ አበባ ያላትን ተሞክሮ የምታካፍልበትን ሁኔታ አስመልክቶ በኢትዮጵያ የአዘርባጃን አምባሳደር ሩስላን ናሲቦቭ እና የዩ ኤን ሀብታት የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ኦውማር ሲላ ጋር ዛሬ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

መድረኩ አዲስ አበባ በዘርፉ ልምዷን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ የምታካፍልበት እና ተሳትፎዋን ይበልጡን የምታሳድግበት ትልቅ አጋጣሚ እንደሚሆን ገልጸዋል።

አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት እንዲሁም የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል ለማድረግ የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም አመላክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.