Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ሲቲ ወልቭስን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ23ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ወልቭስን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የማንቼስተር ሲቲን ግቦች ኦማር ማርሙሽ እና አንቶኒዮ ሴሜኒዮ አስቆጥረዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ማንቼስተር ሲቲ ነጥቡን ወደ 46 ከፍ በማድረግ የሊጉ መሪ አርሰናል ነገ ጨዋታውን እስከሚያደርግ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ማጥበብ ችሏል፡፡
በሌላ የሊጉ ጨዋታዎች ፉልሃም ብራይተንን 2 ለ 1 ሲያሸንፍ በርንሌይ እና ቶተንሃም ሆትስፐር 2 አቻ ተለያይተዋል፡፡
አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ዌስትሃም ዩናይትድ ሰንደርላንድን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወቃል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ምሽት 2 ሰዓት 30 ላይ ቦርንማውዝ በሜዳው ቪታሊቲ ሊቨርፑልን ያስተናግዳል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.