Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ አንድም ብር ብድርና ርዳታ አልወሰደችም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አንድም ብር ብድርና ርዳታ ሳንወስድ ያሳካነው ፕሮጀክት ነው አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፥ ሕዳሴ በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ቁርጠኛ አቋም ተገንብቶ የተጠናቀቀ ግድብ ነው ብለዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በሀገር ውስጥ በውጭ ሀገራትም ያሉ ኢትዮጵያውያን ጨክነው በቁርጠኝነት በጋራ ሆነው ስለሰሩ የተከወነ ፕሮጀክት መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁ የሆነውን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ መገንባቷን ጠቅሰው፥ ነገር ግን በዚህም ሳታበቃ ከአፍሪካ ሦስተኛ የሆነውን የኮይሻ ኃይል ማመንጫ እየገነባቸው ነው ብለዋል፡፡

ከአፍሪካ ትልቁ የሆነው የቢሾፍቱ የአውሮፕላን ማረፊያና የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካን ጨምሮ የግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጀምሯል ነው ያሉት፡፡

በኃይለማርያም ተገኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.