በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች On Feb 3, 2026 77 የኛ ሪፎርም ምን ያህል ትውልድ ላይ አበክሮ እንደሰራ ለማየት አንደኛው መገለጫ ቴክኖሎጂ ነው፤ ከአምስቱ ብዝሃ ዘርፎች አንደኛው ቴክኖሎጂ የሆነበት ምክንያት ውጤቱን በበቂ ደረጃ ባናይም ለትውልድ ለነገ ካለው ፋይዳ አንጻር ነው፤ ከዚህ አንጻር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን መውሰድ ይቻላል፣ ኢትዮጵያ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተቋም ስታቋቁም የትኛውም የአፍሪካ ሀገር በተቋም ደረጃ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን የፈጠረ አልነበረም፣ በሌላውም ዓለም ቢሆን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በፕራይቬት ከሚነገረው ውጪ የመንግሥታት ዋነኛ አጀንዳ አልነበረም፣ በሚቀጥሉት 6/7 ወራት በኋላ የሚደርሰው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ በዓለም ሁለተኛው ነው፤ በዓለም ላይ እስካሁን አንድ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ብቻ ነው ያለው፣ ባለፈው ዓመት ዓመት ተኩል ገደማ ጀምሮ እየተገነባ ያለው እና በመጠናቀቅ ላይ ያለው ዩኒቨርሲቲው በአማካኝ በአንድ ዓመት ውስጥ ስራ ይጀምራል፣ ይህ ዝግጅት የሚደረገው ልክ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ አባቶቻችን በጊዜው በልኩ መስርተውት ዛሬ በአፍሪካ ውስጥ ቀዳሚው እንደሆነው ነገም የኛ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ተቋም እና ዩኒቨርሲቲ የተስተካከለ መሰረት ይዞ እንዲነሳ በሪፎርሙ ውስጥ አንዱና ቁልፍ ጉዳይ አድርገን ስንሰራ ቆይተናል፤ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ብዙ ውጤት አግኝተንበታል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ ለልጆቻችን ውጤታማ ዘመን ይፈጥርላቸዋል። በሶስና አለማየሁ 77 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint