Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ፡፡

በዚህም መሰረት በከተማዋ አሁናዊ ፈጣን ዕድገትና ለውጥ ላይ ተመስርቶ በአምስት ዋና ደረጃዎችና በ30 ንዑሳን ደረጃዎች በቀረበው የቦታ ደረጃ ጥናት መሰረት የተሻሻለ የሊዝ መነሻ ዋጋ ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።

በሌላ በኩል በከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ የተወያየ ሲሆን፥ በከተማዋ ምክር ቤት ለማስጸደቅ እንዲላክ ውሳኔ  አስተላልፏል፡፡

ረቂቅ አዋጁ የከተማዋን የግዢና ንብረት አስተዳደር ሂደትና ስርዓት ለማዘመን፣ የስራ ቅልጥፍናን ለማላቅ እንዲሁም ንብረትን በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች የቀረበ የመሬት ምደባ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.