የኢቤኤስ ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ አማን ፍስሃጽዮን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢቤኤስ ቴሌቪዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ እና መስራች የነበሩት አማን ፍስሃጽዮን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
አቶ አማን ፍስሃጽዮን ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ገልጿል።
አቶ አማን ፍስሃጽዮን ለኢትዮጵያ ሚዲያ ዕድገትና ለኢቢኤስ ስኬት የማይተካ ሚና መጫወታቸው ተገልጿል።