Fana: At a Speed of Life!

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመት ምስረታ በዓል መልካም ምኞቱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ለሚገኘው ዳሸን ባንክ መልካም ምኞቱን ገልጿል።

የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተለያዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎች በዳሸን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ተገኝተው ለተቋሙ ሰራተኞች እና አመራሮች ‘እንኳን ለ30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አደረሳችሁ’ ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የማርኬቲንግና ሽያጭ ሥራ አስፈፃሚ ሰሎሜ አበበ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ተቋማቱ በአጋርነት ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

30ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው ዳሸን ስኬታማ ዓመታትን ማሳለፉን ጠቅሰው፤ በቀጣይ የተሻለ የስኬት ጉዞ እንዲኖረው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የዳሸን ባንክ ቺፍ ስትራቴጂ ኦፊሰር አየለ ተሾመ በበኩላቸው ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከባንኩ ምስረታ ጀምሮ በሚዲያ አጋርነት ሲሰራ የቆየ ተቋም መሆኑን ተናግረዋል።

ፋና ሚዲያ ብዙ ተደራሽነት ያለው፣ በበርካታ ቋንቋዎች የሚሰራ ተቋም መሆኑ ለየት ያደርገዋል ያሉት አቶ አየለ፤ ተቋማቸው ከፋና ሚዲያ ጋር አብሮ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.