Fana: At a Speed of Life!

የፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ጉብኝት የኢትዮጵያ እና ቱርክዬን ስትራቴጂያዊ አጋርነት የሚያጎላ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን የኢትዮጵያ ጉብኝት እያደገ የመጣውን የሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂያዊ አጋርነት የሚያጎላ ነው አለ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፡፡

ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ለፕሬዚዳንቱ አቀባበል አድርገዋል።

ይህ ጉብኝት በኢትዮጵያ እና ቱርክዬ መካከል እያደገ የመጣውን ስትራቴጂያዊ አጋርነት የሚያጎላ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ሚና የሚያረጋግጥ ጉብኝት ነው ብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.