ለምን እንመርጣለን? ምርጫስ ለምን?
🫵 ለምን እንመርጣለን? ምርጫስ ለምን?
በዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ሥርዓት ዜጎች ነጻ የሆነ ሀሳባቸውን የሚገልጹበት እና ሀገርን የሚያስተዳደሩ ብቁ ዕጩዎችን ለሥልጣን የሚያበቁበት አንዱ መንገድ ድምፅ መስጠት ወይም መምረጥ ነው፡፡
ስለዚህም የዜጎች መምረጥ፡-
👉የዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ቁልፍ ጽንሰ ሃሳብ የሚረጋገጥበት፣
👉በህዝብ የተወከለ መንግሥትን የሚያቋቁሙበት፣
👉እኩልነትን የሚያረጋግጡበት፣
👉የሀገር ፍቅርን የሚገልጹበት እና ዘመናዊነትን የሚለማመዱበት፣
👉በሀገራቸው ጉዳይ ላይ የየግል አሻራቸውን የሚያኖሩበት፣
👉የመረጧቸው ተወካዮችን ተጠያቂነትን የሚያረጋግጡበት፣
👉በተለያዩ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ መድረኮች የሚወክላቸውን አስተዳደራዊ አካል የሚመርጡበት፣
👉መንግሥት ለዜጎቹ የሚጠቅም ፓሊሲዎች እንዲያዘጋጅና እንዲተገብር የሚያደርጉበት፣
👉ሃሳብን የመግለጽ እድልን የሚያረጋግጡበት፣
👉የመልካም አስተዳደር መስፈንን የሚከታተሉበት ዓይነተኛ መሳሪያ ነው፡፡
🫵ባለመምረጥ ምን አሉታዊ ተጽዕኖዎች ይከሰታሉ?
👉ሊወክላቸው በማይችል ወኪል መተዳደር፣
👉ባልመረጧቸው እና ባልደገፏቸው የአስተዳደር አካላት ውሳኔ እንዲሁም አስተዳደራዊ ሥርዓት ስር ተገዢ መሆን፣
👉ዜጎች የደገፏቸው የተሻለ የአመራር ሥርዓት ያለው ተወዳዳሪ ተመራጭ አለመሆን፣
ስለዚህ ዜጎች አለመምረጥ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመከላከል የዜግነት መብታቸውን በመጠቀም ድምፅ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡