ኢትዮጵያና ሳዑዲ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር መከሩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዋሊድ አልኬሬጅ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረውን የሁለቱ ሀገራት ጠንካራ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
በተጨማሪም በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጥቅም ላይ በተመሰረቱ ቀጣናዊ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡