Fana: At a Speed of Life!

በሃገር አቀፍ ደረጃ በተጀመረው የኮቪድ 19 የማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄ እና ምርመራ ዘመቻ እንቅስቃሴ ላይ ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በሃገር አቀፍ ደረጃ በተጀመረው የማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄ እና ምርመራ ዘመቻ እንቅስቃሴ ላይ ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡

መንግሥት የ”ማንም” ዘመቻውን በይፋ ካስጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሁሉም አካባቢዎች ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑ በዚህ ወቅት ተገልጿል።

በተግባር እንቅስቃሴ በሁሉም አካባቢዎች ወደ ተስተካከለ አፈጻጸም ለመምጣት የሚያስችሉ ስራዎች መስራት እንደሚጠይቅም በውይይቱ ተለይቷል።

ከወረርሽኙ ስርጭት፣ ስፋት እና ፍጥነት አኳያ የመከላከያ መመሪያዎቹን ዳር እስከ ዳር ተግባራዊ የማድረግ ልምምድ አጠናክሮ ማስቀጠል ወሳኝ እንደሆነ መነሳቱንም በፌስ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.