በኢትዮጵያ አስተማማኝ የዲጂታል ክፍያ ሥነ ምሕዳርን ለማጠናከር…
ለኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማትና የክፍያ ዘርፍ ፈጣሪዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ዲጂታል ንግድን በማሳደግ፣ የደንበኞችን እምነት በማጠናከርና የዘመናዊ የክፍያ መፍትሄዎች ተደራሽነትን በማስፋት ረገድ ድጋፌን አጠናክሬ እቀጥላለሁ አለ ቪዛ፡፡
በዲጂታል ክፍያዎች ዓለም አቀፍ መሪ የሆነው ቪዛ የኢትዮጵያን ዲጂታል ክፍያ ገጽታ ማጠናከር የሚያስችል የአቅም ማጎልበቻ ዓውደ ጥናት አካሂዷል፡፡
የአቅም ግንባታ መርሐ ግብሩ አስተማማኝ የዲጂታል ክፍያ እድገትን ለማፋጠን የኢትዮጵያ ባንኮችን፣ ፊንቴክዎችን እና የክፍያ አጋሮችን ክህሎት ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡
በዓውደ ጥናቱ የኢንዱስትሪ ባለሙያዎችን በማሰባሰብ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አካታችና ቀልጣፋ የዲጂታል ክፍያ ሥነ ምህዳርን መሰረት ባደረጉ በኢኮኖሚክስ፣ ቴክኖሎጂ፣ አደጋ ማዕቀፎችና የአሰራር ምርጥ ተሞክሮዎችን በጥልት ለመመልከት ተችሏል፡፡
ስልጠናው ቪዛ የሀገር ውስጥ እውቀትን ለማስፋትና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በመላ ኢትዮጵያ ለማሳለጥ ባለው ቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ተሳታፊዎች ከመሰረታዊ ክፍያ ሒደት እስከ የንግድ ካርድ መፍትሄዎች ጀምሮ ማስመሰያ (ቶከናይዜሽን)፣ የማጭበርበር አደጋ አስተዳደር፣ የቁጥጥር ተገዢነትና በቪዛ ዳይሬክት የሚደረጉ ፈጣን የገንዘብ ዝውውሮች የመሳሰሉትን የዲጂታል ክፍያ የእሴት ሰንሰለቶች ላይ ግንዛቤ ወስደዋል፡፡
በመድረኩ ጠንካራ እና አካታች የዲጂታል ክፍያ ሥነ ምህዳር ለመገንባት የጋራ እውቀት፣ ትብብር እና ቀጣይነት ያለው ትምህርትና ቁርጠኝነትን እንደሚጠይቅ ተጠቅሷል፡፡
ስልጠናው ባንኮችን፣ ፊንቴኮችን እና የክፍያ አጋሮችን ወደ አንድ ክፍል አምጥቶ ደህንነቱ የተጠበቀ ዲጂታል ንግድን በሚያራምዱ ቴክኖሎጂዎች፣ ኢኮኖሚዎችና የአደጋ ማዕቀፎች ላይ ያለንን ግንዛቤ ማጎልበት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያን ወደ ፊት ለማራመድ ያለው የተሳትፎ ደረጃ እና የጋራ ፍላጎት አበረታች መሆኑን በቪዛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቢሮ አስተዳዳሪ እና ምስራቅ አፍሪካ ክላስተር መሪ ያሬድ እንዳለ ተናግረዋል።
ቪዛ ለኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማትና የክፍያ ዘርፍ ፈጣሪዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ዲጂታል ንግድን በማሳደግ፣ የደንበኞችን እምነት በማጠናከርና የዘመናዊ የክፍያ መፍትሄዎች ተደራሽነትን በማስፋት ረገድ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
http://በኢትዮጵያ አስተማማኝ የዲጂታል ክፍያ ሥነ ምሕዳርን ለማጠናከር…