ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አዘርባጃን ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር በመሆን አዘርባጃን ገብተዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እንዳመለከተው÷ የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጠነከረ መጥቷል።
ለዚህም ጉልህ ማሳያው በጠንካራ ትብብር የቀጠለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሆኑን ጽሕፈት ቤቱ ባወጣው መረጃ አብራርቷል።
ይኸው ላቅ ያለው የሁለቱ ሀገራት ቅርርብን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት መጀመራቸውን አመልክቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር ዛሬ ረፋድ ላይ በባኩ ሄዳር አሊዬቭ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋልም ነው ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት።
በዚህኛው ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ እንደሚያደርስ ይጠበቃል ብሏል።